Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ “የኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄና ባዛር ለመጀመሪያ ጊዜ በቦንጋ ከተማ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ክልላዊ ንቅናቄና ኢግዚቢሽን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ተከፍቷል።

በንቅናቄውና ባዛሩ መክፈቻ የክልሉ ዋና የመንግሥት ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ተገኝተዋል።

የንቅናቄና ባዛሩ ዓላማ በተለይም ወጣቶች እና ሥራ ፈላጊ ሴቶች በስራ ፈጠራ ላይ በስፋት እንዲሰማሩ ግንዛቤ ለመፈጠር የስልጠና ድጋፍ፣ የመስሪያ ቦታ፣ ብድር፣ ገበያ ትስስር እና ሌሎች ድጋፎችን እንዲያገኙ ለማመቻቸት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም ከዉጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የዉጪ ምንዛሪን ማዳንና ወደ ዉጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማምረት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

የንቅናቄና ባዛሩ መከፈት የፈጠራ ስራዎችና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለማስፋፋት እንደሚያስችል የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

የክልሉ ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ባዘጋጀውና ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ክልላዊ ንቅናቄና ባዛር 40 የሚሆኑ በክልሉ የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ለህዝብ እይታ ክፍት አድርገዋል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.