Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ የማሽላ ኢንሼቲቭ አስጀመሩ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ ሶፊ ወረዳ የማሽላ ኢንሼቲቭ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በተጨማሪ የክልሉ ምክትል ርእስ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ወይዘሮ ሮዛ÷ ኢኒሼቲቩ 800 ሄክታር መሬት የሚሸፍንና በ3 ወራት ጊዜ የሚደርስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እንዲሁም በክልሉ ቦለቄ እና ለውዝን ጨምሮ ሌሎች ሰብሎችን ለማምረት በትኩረት እንደሚሰራ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.