Fana: At a Speed of Life!

በንግድ ነፃ ቀጠናዎች አተገባበር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)በንግድ ነፃ ቀጠናዎች አተገባበር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዛንዚባር 14ኛው የአፍሪካ ንግድ ሚኒስትሮች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከመድረኩ በተጓዳኝ ከአለም ነፃ ቀጠና ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳሚር ሃሙሮኒ( ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በንግድ ነፃ ቀጠናዎች አተገባበር ዙሪያ ጠቃሚ ምክክር ማካሄዳቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.