Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 743 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 743 መድረሱን አስታወቀ።

ቢሮው ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 85 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጿል።

በተያያዘም ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ በህክምና ማዕከል ህክምና ሲከታተል የነበረ አንድ ሰው ህይወት ማለፉንም አስታውቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በትናንትናው እለት 109 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል ነው ያለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.