የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በ8ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አደረጉ፡፡
በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን÷ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን አባላቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።
ተማሪዎችም ይህን ማስፈንጠሪያ https://aa.ministry.et/#/result በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡
ፈተናውን ከወሰዱ 85 ሺህ 219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67 ሺህ 903 ያህሉ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣታቸውም ተመላክቷል፡፡
በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡