በኮንሶ ዞን ከ29 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሕገ-ወጥ የወባ መድኃኒቶች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ) በተካሄደ ኦፕሬሽን በኮንሶ ዞን 29 ሚሊየን 172 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው ሕገ-ወጥ የወባ መድኃኒቶች መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑን ጨምሮ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የክልልና የፌዴራል ፖሊስ በጋራ በኮንሶ፣ ጅማ እና አዲስ አበባ ባካሄዱት ኦፕሬሽን የተለያዩ ሕገ-ወጥ የወባ መድኃኒቶች መያዛቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም በኮንሶ ብቻ 29 ሚሊየን 172 ሺህ ብር የሚያወጡ የወባ መድኃኒቶች መያዛቸውን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
ኦፕሬሽኑ በተለያዩ አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠሉንም ነው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ያስታወቀው፡፡