አቶ እንዳሻው ጣሰው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን የማዘመን የሙከራ ትግበራ አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በሰባቱ የክልል ማዕከል ከተሞች ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የማዘመን የሙከራ ትግበራን በቡታጅራ ከተማ አስጀመሩ፡፡
የማዕከላቱ ሥራ መጀመር ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ከወረቀት ነጻ በማድረግ ዲጂታላይዝድ እንዲሆን ያስችላል ተብሏል፡፡
ዘርፉን በማዘመን ረገድም የላቀ ፋይዳ እንዳለው መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የክልል ማዕከል ከተሞች ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ማዘመን የተገልጋዩን ጊዜና ጉልበት ከመቆጠብ ባሻገር ፍትሐዊ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።