Fana: At a Speed of Life!

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ለሐረሪ ክልል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ለሐረሪ ክልል መንግስት የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

በከተማና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የተሠራ የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ማዕከልን ጨምሮ የክረምት በጎ አደራጎት ስራ በክልሉ ተጀምሯል፡፡

እንዲሁም ሚኒስቴሩ 500 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ÷ ለተደረገው ድጋፍ በማመስገን የተጀመረው የልማት ሥራም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው÷ ለሐረሪ ክልል የተደረገው ድጋፍ በጎ አድራጎትን እና የአረንጓዴ ልማት ስራን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቤዛዊት ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.