Fana: At a Speed of Life!

በም/ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም የተመራ ልዑክ በቻይና የሥራ ጉብኝት አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ የተመራ ልዑክ በቻይና የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስና የድሬዳዋ ፖሊስ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት ቤጂንግ ከተማ ሲደርሱ የቻይና የሕዝብ ደህንነት ምክትል ሚኒስትር ሹ ዳቶንግ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ልዑኩ ከቻይና ፐብሊክ ሴኩሪቲ ምክትል ሚኒስቴር ጋር በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና በቻይና በትብብርና በአጋርነት በሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ መክሯል፡፡

በውይይቱ ወቅት ም/ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም ለቻይና ፐብሊክ ሴኪዩሪቲ ሚኒስትር በሚቀጥለው ጥቅምት በሚመረቀው የፎረንሲክ ኢንስቲቲዩት ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ ከኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተላከ የጥሪ መልዕክት አድርሰዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ከቻይና ፐብሊክ ሴኪዩሪቲ ዩኒቨርሲቲ ሊቀመንበር ዜንግ ሂያ ጋርም በስልጠና ዙሪያ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ባደረጓቸው ውይይቶች በኢትዮጵያና በቻይና መካከል የእህትማማች የፖሊስ ከተሞችን ለማገናኘት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.