Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎቱ በገዜ ጎፋ ወረዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የአገልግሎቱ ምክትል ጀነራል ዳይሬክተር ርስቱ ይርዳ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በሥፍራው ተገኝተው አጽናንተዋል፡፡

የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሁለት ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

በአካባቢው ስጋት ያለባቸው ዜጎች መንግስት በሚያመቻቸው አማራጭ ከስጋት ቀጣናው እንዲወጡ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ፣ ማቱሳላ ማቴዎስ እና መለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.