Fana: At a Speed of Life!

ግብረ-ኃይሉ ወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታን ገምግሞ አቅጣጫ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ ሀገራዊ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታን ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል÷ የጋራ ግብረ-ኃይሉ በኢትዮጵያ እየተሻሻለ የመጣውን የፀጥታ ሁኔታ አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ የሚጠብቁ ሁነቶች በሰላም እንዲካሄዱ ከወዲሁ ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ ለተግባራዊነቱ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

አሁን ላይ የተገኘውን ሰላም አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሁነቶችን ሰላምና ደኅንነት የማረጋገጥ አቅጣጫዎችን አስቀምጦ ውይይቱን ማጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.