ለአትሌት ኮንስታብል ደሬሳ ገለታ የማዕረግ እድገት ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ በወንዶች ማራቶን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከተው እና 5ኛ ደረጃ በመያዝ በዲፕሎማ ላጠናቀቀው አትሌት ደሬሳ ገለታ የማዕረግ እድገት ሰጠ።
በዚሁ መሠረት ለአትሌቱ የረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ መሰጠቱን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤልም ለአትሌቱ ማዕረጉን አለልብሰዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም በቀጣይ ለኦሜድላ ስፖርት ክለብ በይበልጥ ትኩረት በመስጠት ለ34ኛው ኦሊምፒክ ስፖርተኞችን በማሳተፍ ከዘንድሮው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ይሠራል ብለዋል፡፡