በሲዳማ ክልል አጀንዳዎችን ወደ ባለ ድርሻ አካላት የሚወስዱ 60 ወኪሎች ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ተሳታፊ የማኅበረሰብ ተወካዮች አጀንዳዎቻቸውን በአደራ መልክ ወደ ባለ ድርሻ አካላት የሚያደርሱ 60 ወኪሎች ተመረጡ።
በክልሉ ከ45 ወረዳዎች የተወጣጡ 920 የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ከየአካባቢዎቻችው በአመጡት አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ ቆይተዋል፡፡
ባደረጉት ምክክርም ደርሰንበታል ያሉትን የመጨረሻ አጀንዳዎቻቸውን በማደራጀት በአደራ መልክ ይዘው ወደ ባለድርሻ አካላት የሚሄዱ 60 ወኪሎችን ከመካከላቸው መርጠዋል።
የተመረጡት ወኪሎችም ነሐሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በሚጀምረው የባለድርሻ አካላት ምክክር ላይ አጀንዳዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡
ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው ውይይትም የሚመለከታቸው አካላት በጋራ መክረው የሲዳማ ክልል አጀንዳ ተደራጅቶ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሚሰጥ ይሆናል፡፡፡
በፍቅርተ ከበደ፣ ጀማል ከዲሮ እና ታመነ አረጋ