በዓዲ-ዳዕሮ ከተማ 18 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለአገልግሎት በቃ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የዓዲ-ዳዕሮ ከተማ 18 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአገልግሎት መስጠት መጀመሩን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ተወካይ ኃላፊ ኢንጂነር ዮሃንስ መለሰ በዚህ ወቅት÷ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቃው ዋን ዋሽ ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በተገኘ 57 ሚሊየን ብር ወጪ ነው።
ፕሮጀክቱ ከ6 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር በላይ የቁፋሮ እና የውኃ ቱቦ መስመር ዝርጋታ ሥራዎችን በማከናወን ለአገልግሎት እንዲበቃ መደረጉ ተገልጿል፡፡
የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ 18ሺህ 500 የሚሆኑ የዓዲ ዳዕሮ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።