ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ጂን ሊኩን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱም በኢትዮጵያ እና በባንኩ መካከል ሊኖር ስለሚችለው የአረንጓዴ ኢነርጂ፣ አቪዬሽን እና መሠረተ ልማት ትብብር ዙርያ ያተኮረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ገልፀዋል፡፡