ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ወደ ሕብረተሰቡ ሊሰራጭ የነበረ በርበሬ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተበላሸና ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ወደ ሕብረተሰቡ ሊሰራጭ የነበረ በርበሬ መያዙ ተገለጸ፡፡
በርበሬው የተያዘው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ በሚገኝ መጋዘን ውስጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ በርበሬ እያዘጋጀ ለሕብረተሰቡ እንዲያከፋፍል ከምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፈቃድ እንዳልተሰጠውና የጥራት ማረጋገጫ ሠነድ እንደሌለው ተገልጿል፡፡
በርበሬው ወደ ሕብረተሰቡ ተሰራጭቶ ቢሆን ኖሮ ከፍተኛ የጤና ጉዳት እንደሚያስከትልም ተመላክቷል፡፡