Fana: At a Speed of Life!

በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምሥጋና ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ 19ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በታሰበው መሠረት በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምሥጋና አቀረቡ፡፡

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል፡፡

ይህን ተከትሎም አቶ ጥላሁን ባስተላለፉት የምሥጋና መልዕክት÷ በዓሉ በታሰበው ልክ በብቃት ተዘጋጅቶና በድምቀት ተከብሮ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከቅደመ ዝግጅት ጀምሮ ሥራውን በማስተባበር ለውጤት ላበቁ ተቋማት፣ በየደረጃው ላሉ አመራሮች፣ ለፀጥታ አካላትና ለሚዲያ ተቋማት ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የበዓሉን ዝግጅት በቅርበት በመከታተልና በማገዝ ጉልህ አስትዋጽኦ ላበረከቱት የፌደሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች የምክር ቤቱ አመራሮች እንዲሁም የበዓሉ ታዳሚዎችን አመሥግነዋል፡፡

እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ ቆይታቸው ያማረ እንዲሆን ላደረጉ የጋሞና ወላይታ ዞን ሕዝቦችን፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎችን፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲንም አመሥግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.