በአማራ ክልል ለጤናው ዘርፍ ተግዳሮት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በክልሉ በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ በሚገኙ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የወባ በሽታ ስርጭትን መከላከልና መቆጣጠር በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ እንዲሁም በክልሉ እየተካሄደ ባለው የኮሌራ በሽታ ክትባት ሒደት ዙሪያ መክረዋል፡፡
ክልሉ በጸጥታ ችግር ውስጥ የቆየ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለይም ለጤናው ዘርፍ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን መፍታት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ በክልሉ የጤና ተደራሽነትና ተያያዝ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።