Fana: At a Speed of Life!

ወታደራዊ ቅርሶችን የመሰብሰብና ታሪኮችን የመሰነድ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ቅርስና ጥናት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወታደራዊ ቅርሶችን የመሰብሰብና ታሪኮችን የመሰነድ ስራ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

የአስተዳደሩ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ደሳለኝ ደቼ ÷ ኢትዮጵያ ሰፊ ወታደራዊ ቅርስ ፣ባህልና ታሪክ እንዳላት አንስተው ይህም የሀገርን ታሪክና ባህል ከመዘከር ባለፈ ሠራዊቱ የድልና የአሸናፊነት ምንጭ የመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በተቋሟዊ ሪፎርም ትግበራ የተቋቋመው የመከላከያ ቅርስና ጥናት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወታደራዊ ቅርሶችን በመሰብሰብ ፣በሰው ሀይል በማደራጀት ፣ ታሪኮችን በመሰነድና በማጥናት እንዲሁም አውደ ርዕይ በማዘጋጀት በርካታ ተግባራን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ነው የገለጹት ፡፡

በተጨማሪም ዳይሬክቶሬቱ የዘመናዊ ወታደራዊ ሙዚየም ህንፃ ዲዛይን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንደ ሀገር የሚገነባው ዘመናዊ ወታደራዊ ሙዚየም ከሠራዊት ግንባታ ባሻገር ለትውልዱ የሚተላለፍና በቱሪዝም ዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ፈይዳ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.