ስማርት ጂግጂጋ ፕሮጀክትን ለመተግበር ያለመ ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና የጂግጂጋ ከተማ አሥተዳደር ስማርት ጂግጂጋ ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር ታሪኩ ደምሴ እና የጂግጂጋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሻፊ አሕመድ (ኢ/ር) ናቸው፡፡
በስምምነቱ ወቅት ከንቲባው እንዳሉት÷ በከተማዋ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት እውን መደረጉ የጂግጂጋን ዕድገት ለማላቅ ያግዛል።
አቶ ታሪኩ በበኩላቸው በተለያዩ ዘርፎች እየተደረጉ የሚገኙ የዲጂታላዜሽን ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ስማርት ሲቲ ፕሮጀክትም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሳደግና የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል እያገዘ ነው ብለዋል።
ስማርቲ ሲቲ ፕሮጀክት ቀደም ሲል አዲስ አበባን ጨምሮ በዘጠኝ ሌሎች ከተሞች ተግባራዊ መደረጉ ይታወሳል።
በተስፋዬ ኃይሉ