Fana: At a Speed of Life!

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የበጀት ዓመቱን የስኳር ምርት ሥራ ጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የ2017 ዓ.ም የስኳር ምርት ሥራውን በመጀመር ከታሕሣሥ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስኳር በማውጣት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የፋብሪካው የክረምት ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ፈይሳ ፍቃዱ፣ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት አገዳ የመፍጨት ሥራውን እንደጀመረ ከግሩፑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሚገኙት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 እና 3 ስኳር ፋብሪካዎች በአካባቢው ካለው የአየር ንብረት ጋር በተያያዘ የማምረቻ ጊዜያቸው በዓመት ሁለት ጊዜ መሆኑ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.