Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤም ለፕሬዚዳንት ማክሮን የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የዓድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውን እና ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ትግል መስዋዕት በከፈሉ ጀግኞች መታሰቢያ ሀውልት ሥር የአበባ ጒንጉን ማስቀመጣቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ባሳየችው ፈጣን ለውጥ አድናቆታቸውን እንደገለጹላቸውም ከንቲባዋ አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.