ኮሚሽኑ የኦሮሚያ ክልልን አጀንዳ ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልልን አጀንዳ ተረክቧል፡፡
ኮሚሽኑ በአዳማ ከተማ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ አጠናቅቋል፡፡
በዚህም ከአምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ 25 ወኪሎች አጀንዳዎቹን አደራጅተው ለኮሚሽነሮች ያስረከቡ ሲሆን ፥ የአጀንዳ አሰባሰብ ምዕራፉ ነፃና ግልጽ ሆኖ መጠናቀቁን ዋና ኮሚሽነሩ መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ተናግረዋል።
ውይይቶቹ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ሳይኖርባቸው አጀንዳዎች ተደራጅተው ለኮሚሽኑ ርክክብ መደረጉንም ጠቅሰዋል።
በመራኦል ከድር እና አሸናፊ ሽብሩ