ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሽብርተኝነትን በጋራ መከላከል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መከሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሽብርተኝነትን ጨምሮ የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ መካላከል በሚችሉበት አግባብ ላይ ምክክር ተደረገ፡፡
የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በናይሮቢ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም እንደ ሽብርተኝነትና የተደራጁ ወንጀሎች ያሉ የደኅንነት ችግሮች በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ባሉ ሀገራት መካከል መተባበርን እንደሚጠይቅ ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡
ለዚህም ኬንያ መረጋጋትን ለማምጣት ከአጋሮቿና ከሀገራት ጋር እንደምትሰራ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ አረጋግጠዋል፡፡