Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት ለጎንደር የሚሰስተው ነገር የለም – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት ለጎንደር ከተማ የሚሰስተው ነገር የለም ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከጎንደር ከተማ ነዋሪ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የፌዴሽን ምክርቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተገኝተዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፥ በከፍተኛ አመራሮቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎንደር ሕዝብ ለዘመናት ሲያነሳቸው የነበሩ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እያደረጉ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ በምላሻቸው አስረድተዋል፡፡

መንግስት ጎንደር በታሪኳ ልክ የከፍታና የዕድገት መሻቷን እንድታሳካ በሁሉም መስክ አበክሮ እየሠራ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

የጎንደር መለወጥና የሕዝቡ በልማት ተጠቃሚ መሆንን የማይፈልጉ አካላት አካባቢው ሰላም እንዳያገኝ ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

ይህን አካሄድ ቀድሞ የተቃወመውና ያከሸፈው የጎንደር ሕዝብ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፥ ሰላምና ልማትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በጋራ መሥራት እንደሚገባ አአሳስበዋል፡፡

ችግሮች ሲኖሩ በሰላማዊ ውይይት የመፍታት ባህልን በማጎልበት መፃኢ ዕድሎችን በጋራ መተለምና ማሳካት የትውልዱ ኃላፊነት መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.