Fana: At a Speed of Life!

የቱሪዝም ዘርፉ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው – ሰላማዊት ካሣ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከከብልጽግና ፓርቲ ምስረታ ወዲህ በመጣዉ የእይታ ለውጥ የቱሪዝም ዘርፉ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሣ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ፥ ለውጡን ተከትሎ በዘርፉ የተወሰዱ የፖሊሲ ለውጦች የመዳረሻ ልማቶችን ያሰፋ፣ ዘርፉ ይበልጥ ትኩረት እንዲያገኝ ያስቻለ፣ ተሸፍነው የነበሩ ሀገራዊ ሀብቶች እንዲወጡ በማድረግ የኢትዮጵያን አስደናቂ ውበት የገለጠ ነው ብለዋል፡፡

በተለይ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን መገንባትና ነባሮችንም ዘመኑ በሚጠይቀው ልክ የማደስ ተግባር ዘርፉ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ቀልብ እንዲስብ ማስቻሉን አብራርተዋል።

በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት የቱሪስት መዳረሻዎች ያሰፋና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሠረተ ልማቶች የተገነቡበት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ሁሉን አካባቢዎች ማዕከል በማድረግ የተከናወኑና በመከናወን ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ እምቅ ሃብቶች ጎልተው እንዲታዩ ያስቻሉ እንደሆኑም ነው ሰላማዊት ካሳ የገለጹት፡፡

የጨበራ ጩርጩራ፣ ሀላላ ኬላ፣ ጎርጎራና የወንጪ ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክቶችን ጠቅሰው፥ እነኚህም የቱሪዝም ዕይታን ያሰፉና ተግባራዊ ውጤቶችም የተገኙባቸው መሆናቸው ይታወቃል::

ከመዳረሻ ልማቶቹ ባሻገር በቱሪዝም ዘርፉ የተከናወኑ የፖሊሲ ለውጦች በዘርፉ ላይ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲመጡ ማስቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በውጭ ሀገራት የኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻዎች የማስተዋወቅ የጎብኚዎችን ቁጥር ለመጨመር አበረታች ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

በዲጂታሉ ዓለም የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን መግለጻቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.