Fana: At a Speed of Life!

ሕብረቱ በመከላከያ መስኮች እየተደረጉ ያሉ ሪፎርሞችን እንደሚደግፍ አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ በፀጥታና ደኅንነት ተቋማት እያደረገች ያለውን ጥረትና ስኬቶች በተመለከተ ሚኒስትሯ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በተለይም በመከላከያ ሪፎርም፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ባላት ግንኙነትና፣ የሰላም ማስከበር ሚናዋን በተመለከተ አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደር ሶፊ ፍሮም በበኩላቸው ኢትዮጵያ በተለይም በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላት የቆየ ልምድና መልካም ስም የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከጎረቤቶቿ ጋር ያላትን የሰላም፣ ትስስርና ጉርብትና ለማጠናከር እየወሰደቻቸው ያሉ ርምጃዎችን ሕብረቱ ያደንቃል ብለዋል፡፡

ሕብረቱ  በመከላከያ መስኮች እየተደረጉ ያሉ ሪፎርሞችን ለመደገፍና ለማገዝ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.