Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ አሥተዳደር የዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

የተፋሰስ ልማት ሥራው “የአፈር ጥበቃ ስራችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ሐሳብ በ38 የገጠር ቀበሌዎች ላይ ተጀምሯል።

የአሥተዳደሩ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ፈትያ አደንና ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች የተፋሰስ ሥራውን ማስጀመራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዛሬ በተጀመረውና ለአንድ ወር በሚዘልቀው የተፋሰስ ልማት ሥራ 5 ሺህ 550 ሄክታር የተራቆቱ አካባቢዎች የአፈርና የውሃ ጥበቃ ሥራ እንደሚከናወን የድሬዳዋ ግብርና፣ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኑረዲን አብደላ ገልጸዋል፡፡

የገጠር መንገድ ጥገና፣ የመስኖ ውሃና የማሳ እንክብካቤ፣ የጤና እና የትምህርት ተግባራትን ከፍ የሚያደርጉ ስራዎች እንደሚተገበሩም ጠቁመዋል፡፡

የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው የመሬት መራቆትን ይቀንሳል፤ በጎርፍ የሚወሰድ 48 ሺህ 700 ቶን ለም አፈርንም ይታደጋል ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ 41 ሺህ 300 የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በባለቤትነት በሥራው ላይ እንደሚሳተፉም ነው የተመላከተው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.