Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከበጋ መስኖ 817 ሺህ ኩንታል ምርት ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከበጋ መስኖ  እስካሁን 817 ሺህ ኩንታል ምርት መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮው የመስኖ ልማት ዳይሬክተር አቶ እስራኤል ኢዮብ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ ባለፉት 6 ወራት በክልሉ የበጋ መስኖ ልማትን ይበልጥ ለማስፋፋት በትኩረት ተሰርቷል፡፡

በዚህም መሠረት ለበጋ መስኖ ልማት ምቹ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት ልማቱን የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 59 ሺህ 104 ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት መታቀዱን ጠቁመው፥ አሁን ላይ 24  ሺህ 668 ሄክታር መሬት በመስኖ መልማቱን ተናግረዋል።

በበጋ መስኖ ከለማው መሬትም እስካሁን 817 ሺህ ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ነው ያስረዱት።

የበጋ መስኖ ልማትን ለማፋጠን የተለያየ አቅም ያላቸው የመስኖ ግድቦች ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አንስተዋል።

በክልሉ 19 አነስተኛ የመስኖ ግድቦችን ለመገንባት መታቀዱን ገልጸው፥ ከዚህ ውስጥ የ13ቱ ግድቦች ግንባታ ሥራ መጀመሩን አመልክተዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.