Fana: At a Speed of Life!

የምርጫው ውጤት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምርጫው ውጤት የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትእና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የፓርቲው ፕሬዚዳንት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ ዛሬ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የብልፅግና ፓርቲን ምርጫ አካሂደናል ብለዋል።

ይኽም ወደ ዲጂታል ሽግግር የምናደርገው የሀገራዊ ጉዞ አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በምርጫው ውጤት በእኔና በምክትል ፕሬዝዳንቶች የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነውም ብለዋል።

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ከፍተኛ በሆነ ድምጽ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ የመረጠ ሲሆን አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች አድርጎ መርጧቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.