Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የልዕልና ጉዞ እናሳካዋለን – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የልዕልና ጉዞ እናሳካዋለን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ ብልፅግና ፓርቲ የጠራ ሃሳቡንና ትክክለኛ ፖሊሲዎቹን በትጉህ አመራርና አባላቱ በመፈጸም በአስደማሚ ድሎች ጉዞውን መቀጠሉን ጠቁመዋል።

ፓርቲያችን ከእነዚህ ድሎች ማግስት ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ሀገርና ህዝብን እንድናገለግል አደራ ተሰጥቶናልም ነው ያሉት።

በዚሁ መሠረት እኛም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እና የህዝባችንን መሻት ለማሳካት ቃላችንን በድጋሚ አድሰናል ሲሉም ገልጸዋል።

ሁለንተናዊ ክብርና ብልፅግናን የተቀዳጀች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ለፈተናዎች ሸብረክ ሳንል ያለ እረፍት እንደምንሠራ ለመላው ህዝባችን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ ሲሉም የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ቃል ገብተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.