Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የወጣቶች የሰላምና ደህንነት ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር አቀፍ የወጣቶች የሰላምና ደህንነት ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው

የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የሥነ-ህዝብ ልማት ፈንድ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ኮንረንሱ “ወጣት የሰላም ባለቤት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመርሐ-ግብሩየሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስትር አቶ መሃመድ እድሪስ፣ በተባበሩት መንግስታት የሥነ-ህዝብ ልማት ፈንድ ተወካይ ኮፊ ኮዮሜ፣ ሚኒስትር ዴዔታዎች እንዲሁም ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

መድረኩ ወጣቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና እና ሰላምን ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ሃሳቦች ላይ ለመመካከር ያለመ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.