Fana: At a Speed of Life!

ከ21 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ባላፉት 6 ወራት 21 ሺህ 104 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል፡፡

ደንበኞቹ 6 ሺህ 455 በኦሮሚያ፣ 6 ሺህ 306 በአማራ፣ 2 ሺህ 374 በትግራይ፣ 288 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ 64 በጋምቤላ እና በሌሎች ክልሎች የሚገኙ ናቸው ተብሏል፡፡

ደንበኞችን ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 639 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 1 ሺህ 61 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር እና 245 ትራንስፎርመር ተከላ ስራ መከናወኑ ነው የተገለጸው፡፡

በተመሳሳይ በዋናው የኃይል ቋትና በፀሐይ ኃይል ምንጭ የገጠር ከተሞችን በማገናኘት አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተነግሯል፡፡

ተቋሙ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን አማራጭ የኃይል ምንጮችን በመጠቀም ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.