የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡
በግምገማ መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን እና የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የክልሉ መንግስት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ባለፉት ስድስት ወራት በልማት እና በመልካም አስተዳደር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ላይ ትኩረት አድርጎ ግምገማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶች፣ የተገኙ ተሞክሮዎችና የታዩ ክፍተቶች ላይ በጥልቀት ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡
በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ የትኩረት አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅምየክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡