Fana: At a Speed of Life!

13 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአራት ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) የ2017/18 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ግዥን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው መንግስት ለግብርናው ልዩ ትኩረት መስጠቱን ተከትሎ በዘርፉ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡

መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት ከሚሰራባቸው ጉዳዮች አንዱ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የማስገባት ሥራ በከፍተኛ ትጋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 24 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ለመፈፀም ታቅዶ 13 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል ግዥ መፈፀሙን ተናግረዋል።

ከተገዛው 13 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል ውስጥ 6 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል የሚሆነው ጅቡቲ ወደብ መድረሱን አመልክተዋል፡፡

አሁን ላይም ከ4 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ሚኒስትር ዴዔታዋ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.