Fana: At a Speed of Life!

ብሄራዊ ገዥ ትርክትን ለማስረጽ በትኩረት መስራት ይገባል – አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ፓርቲው በተለይም ከመጀመሪያው ጉባዔው ጀምሮ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች በርካታ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል።

ክልሉ ሕዝቡን በማሳተፍ ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት ቀዳሚ አጀንዳ ተደርጎ ሲሰራ ቆይቷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የሕዝቦችን አብሮነት እና አንድነትን በማጎልበት የገዥ ትርክት ግንባታን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ፣ በቤተሰብ ደረጃ ብሎም እንደ ሀገር ተጨባጭ ብልፅግናን እውን ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በክልሉ ሕገ-ወጥ የንግድ እና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ በመግታት ጤናማ የንግድ ስርዓት እንዲዘረጋ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በከተሞች የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ፣ ውብ፣ ፅዱና ተስማሚ እንዲሆኑ የትኩረት አቅጣጫ ስለመደረጉም ጠቅሰዋል።

በቅድመ መደበኛ የትምህርት ደረጃ ላይ አበክሮ በመስራት ተማሪዎችን በትምህርት ገበታ ማቆየት እንደሚገባ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጤና፣ በቱሪዝም፣ በሴቶች፣ በወጣቶች እና በሌሎች ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ይሰራል ብለዋል።

የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢስሃቅ አብዱልቃድር በበኩላቸው፣ብልጽግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባዔው ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በቁርጠኝነት በመፈጸም የሕዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.