በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የግብርና የልማት ሥራዎች አበረታች ናቸው- ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተቋማት እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸው የግብርና ሚኒስትርሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ከሌሎች የፌዴራልና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል እና በቦንጋ ዩኒቨርስቲ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ፥ በቦንጋ የግብርና ምርምር ማዕከል እየተከናወኑ ያሉ የዘር ብዜት ስራዎች እና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በማዕከሉ የተከናወኑ የልማት ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው ፥ ሚኒስቴሩ በተቋሙ እንደማነቆ የቀረቡ ጉዳዮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ በተቋማቶቹ እየተሰራ ያለው ተግባር ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፤
የክልሉ መንግሥት በማዕከሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የየልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡