Fana: At a Speed of Life!

በመርሐቤቴ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መርሐቤቴ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው የማገዶ እንጨት የጫነ የጭነት ተሽከርካሪ ከላይ 25 ሠራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ በመገልበጡ ነው የደረሰው፡፡

በተከሰተው አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ም/ኮማንደር የሺዓለም እንደሻው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በ15 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰ መግለጻቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.