Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 7ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የክልሉ መስተዳድር ም/ቤት የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በሚቀርቡ የተለያዩ አጀንዳዎች፣ አዋጆች እና ተጨማሪ ረቂቅ በጀት ላይ በመምከር ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

በጉባዔው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላምን ጨምሮ የክልሉ ም/ቤት አባላት፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በተስፋዬ ሀይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.