Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በክላውድ አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ የዲጂታል ሶሉሽኖችን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የድርጅት ደንበኞችን እና ተቋማትን አቅም የሚገነቡ እና የሚያዘምኑ በክላውድ አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ ሰባት የዲጂታል ሶሉሽኖችን በይፋ አስጀምሯል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በዚህ ወቅት ÷ ዲጂታል ሶሉሽኖቹ ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ለህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ለውጥና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ትልቅ ትርጉም የሚያመጡ ናቸው ብለዋል፡፡

ኢቲዮ ቴሌኮም የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን እና የፋይናንሺያል አካታችነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መጠነ ሰፊ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ ላይ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የተቋማትን አሰራር የሚያዘምኑና ለደንበኞቻቸው የላቀ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችሉ በክላውድ ሶሉሽን የታገዙ ሰባት የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖችን ይፋ አድርገዋል፡፡

የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖቹም ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ፣ ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ፣ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን፣ የትምህርት አመራር ስርዓት ሶሉሽን፣ የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት ሶሉሽን ፣ ቴሌ ኮንታክት ሴንተር እና ኢ.አር.ፒ ሶሉሽኖች የተሰኙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዘቢብ ተክላይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.