Fana: At a Speed of Life!

የጠ/ሚ/ጽ/ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በኢንስቲትዩቱ የበለፀጉ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቴክኖሎጂ ሥራዎችን የገመገመ ሲሆን፤ በተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎችንም ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች በተመለከተ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጻ አድርገዋል፡፡

የሱፐርቪዥን ቡድኑ መሪ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት፤ ኢንስቲትዩቱ ከዕድሜው በላይ የሆኑ ሥራዎች ሠርቷል፤ ተቋሙ ለሀገርም ትልቅ ዐቅም ነው ብለዋል፡፡

ይህን ዐቅም በተለያዩ ዘርፎች ለሚታዩ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅርበት መሥራት ይገባል ማለታቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላጀክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.