Fana: At a Speed of Life!

72 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሰባት ወራት 72 አዳዲስ የገጠር መንደሮችና ከተሞችን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
አገልግሎቱ በዋናው የኤሌክትሪክ መረብ 69 እንዲሁም በኦፍ ግሪድ በጸሃይ ኃይል ማመንጫ 3 ከተሞችን ነው የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ማድረግ የቻለው፡፡
ለዚህም 750 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የዝቅተኛ መስመር እንዲሁም 300 የተለያዩ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች መተከላቸው ተጠቁሟል።
በተከናወነው ሥራም ከ24 ሺህ በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.