የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዓለ ሢመት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ 12ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግሥት አመራሮች፣ አምባሳደሮች እንዲሁም የገዳማትና አድባራት ሊቃውንትና ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ፈጣሪ የሾመን ሰላምን እንድናውጅ፣ ፍትሕና ርትዕ አንዳይዛባ እንድንመክር፣ አንድነት፣ እኩልነት፣ ፍቅርና ይቅርታን እንድናስተምር ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና መላው ሕዝበ ክርስቲያን ለሰላም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በርትተው ሊሰሩ እንደሚገባም ብፁዕነታቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በሰማኸኝ ንጋቱ