የጎሬ-መቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እየተፋጠነ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የጎሬ-መቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ የተመራ የፕሮጀክቶች ድጋፍ እና ክትትል ቡድን የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክትን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል።
ግንባታው ከተጀመረ ሁለት ዓመት የሆነው አውሮፕላን ማረፊያው በአሁኑ ወቅት አፈጻጸሙ 69 በመቶ መድረሱ ተነግሯል፡፡
ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግ የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ ማረጋገጡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል፡፡