የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች መንግስት የሀገሪቱን ዜጎች ወደ ብልጽግና ማማ የሚያሻግሩ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የኢትዮጵያን እድገት እና ስኬት የሚያሳይ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ሌሎች ሥራዎችን በመስራት የኢትዮጵያን ገጽታ ይበልጥ ማስተዋወቅ እንደሚገባ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
መንግስት እያከናወነ ያለውን ሥራ ያደነቁት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች÷በአንድነትና በትብብር ተጨማሪ ድሎችን ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ለተከታታይ አስር ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡