አምባሳደር ዑመር (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለዮርዳኖስ ንጉስ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ ዮርዳኖስ እና ሶሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለዮርዳኖስ ንጉስ አብደላህ 2ኛ አቅርበዋል።
አምባሳደሩ በዚህ ወቅት÷ከኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለዮርዳኖስ መንግስትና ሕዝብ የተላለፈ የሰላምታና መልካም ምኞት መልዕክትን አድርሰዋል፡፡
አምባሳደር ዑመር (ዶ/ር)÷በኢትዮጵያ እና ዮርዳኖስ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ንጉስ አብደላህ 2ኛ በበኩላቸው÷ለአምባሳደሩ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መመኘታቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሁለቱን ሀገራት በሁሉም ዘርፎች ይበልጥ ለማስተሳሰር አምባሳደሩ ለሚያከናውኑት ሥራ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል።