የኢጋድ ቀጣናዊ ሰላምና ደህንነት ስብስባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት ስብስባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የኢጋድ የሰላም እና ደህንነት ፕሮግራም ዳይሬክተሮች እንዲሁም ልዩ ልዑኮች እና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።
ስብሰባው ኢጋድ በፈረንጆቹ 2025 እና 2026 በሰላምና ደህንነት ዘርፍ የቅድሚያ ትኩረት የሰጣቸውን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ከአጋር አካላት ፍላጎቶች ጋር አጣጥሞ ማስኬድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የትብብር ማዕቀፉ ኢጋድ ለቀጣናው መረጋጋት፣ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል እና የዲፕሎማሲ መፍትሄዎችን ገቢራዊ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ መገለጹን የኢጋድ መረጃ ያመላክታል።