የቻይና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጥናት ተቋም ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መሥራት እንደሚፈልግ ገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጥናት ተቋም ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር መሥራት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
በተቋሙ የታዳጊ ሀገራት ዲፓርትመንት ልዑክ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ጥናትና ምርምር ዘርፍ በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡
በተጨማሪም ኮንፈረንሶችን እና ውይይቶችን በጋራ ማዘጋጀት የሚችሉበትን የትብብር ስምምነት ለመፈረም እና የወደፊት አጋርነትን ለማጠናክር የሚያስችል ምክክር አድርገዋል፡፡
የተቋማቱ በተብብር ለመሥራት የሚያስችል ምክክር፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና ያላቸውን ዘርፍ-ብዙ ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል መባሉን የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላክቷል፡፡