ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በአርሲ ዞን የወጣቱን ሰላም የማስጠበቅ ሥራ አደነቁ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ትናንት ምሽት በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ጎራ ሲሊንጎ ቀበሌ እና አንጋዳ ከተማ ከሚገኙ የሃገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች ጋር አብረው አፍጥረዋል።
ከአፍጥር ሥነ-ሥርዓቱ ጎን ለጎንም በአካባቢው ልማት እና ሰላም ጉዳይ ዙሪያ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷የአካባቢው ሕዝብ በተለይም ወጣቱ ሰላምን ለማስጠበቅ እየተጫወተ ላለው ተምሳሌታዊ ሚና አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል።