Fana: At a Speed of Life!

ደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የድሮን ቴክኖሎጂን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በእውቀት የተገነባ ትውልድ ከማፍራት ባለፈ በምርምና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለሀገር የሚጠቅሙ ሥራዎችን እያበረከተ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ሬዳ ናሞ (ዶ/ር)÷ዩኒቨርሲቲው በግብርና ዘርፍ፣ በድሮን ቴክኖሎጂ፣በጤና እና ሌሎች ዘርፎች የምርምር ሥራዎችን በማከናወን የድርሻውን እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በድሮን ቴክኖሎጂም ለውጤት የሚበቃ ሥራ ላይ እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው÷የተማሪዎችን የምግብ ፍጆታ በራስ አቅም ለመሸፈን የተቀናጀ የግብርና ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በምርምር ሥራው ሀገርና ሕዝብን የሚጠቅሙ ተግባራትን ማከናወኑን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል፡፡

ደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝነት በመሸጋገር ራሳቸውን እንዲችሉ በመንግስት በተቀመጠው አቅጠጫ መሰረት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው በተጓዳኝ በተለይም በጥናትና ምርምር እንዲሁም ማህበረሰባዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.